ኤቨርተን ከማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል-የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ግምቶች

የሳምንቱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ በሜዳው ሊቨርፑልን የሚያስተናግድበት ነው።
የሊጉን ዋንጫ መዳረሻ በመወሰን ረገድ ግን ማንቸስተር ሲቲ ወደ ዲኪንሰን አቅንቶ ኤቨርተንን የሚገጥምበት ጨዋታ ትልቅ ትኩረት አግኝቷል።
"ይህ ጨዋታ ለሲቲ የዋንጫ ግስጋሴ ትልቁ ፈተና መሆኑን" የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ገምቷል።
ሱተን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኞ የሚደረጉ ጨዋታዎችን እንደሚከተለው ገምቷል።
አርብ
ሊድስ ከ በርንሌይ
በርንሌይ ከሊጉ ከመውረዱም በላይ አሰልጣኝ ስኮት ፓርከር ከቀናት በፊት ከቡድኑ ተለያይቷል።
ሊድስ ደግሞ ጥሩ የውድድር ዓመት እያሳለፈ ነው።
ቡድኑ በዚህ ጨዋታ ከተሸነፈ ቀጣይ ከቶተንሃም እና ዌስት ሃም ጋር ከባድ ፈተና ይገጥመዋል።
በዚህ ጨዋታ ቡድኑ አለመውረዱን የሚያረጋግጥ ይመስለኛል።
ግምት፡ 2 - 0
ቅዳሜ
ብሬንትፎርድ ከ ዌስት ሃም
ዌስት ሃም ባለፈው ሳምንት አስፈላጊ የተባለ ድል ኤቨርተን ላይ አስመዝገቧል።
ቡድኑ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ጥሩ ቢንቀሳቀስም ውጤቱ ግን በሚጠበቀው ልክ አልሆነም።
ብሬንትፎርድ ባለፈው ሳምንት ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር አንድ ነጥብ እንኳን አለማሳካቱ ዕድለ ቢስ ያደርገዋል።
ግምት፡ 1 - 1
ኒውካስል ከ ብራይተን
ኒውካስል በሊጉ ለመቆየት ሁለት ነጥቦች ያስፈልጉታል።
ቡድኑ በሊጉ የሚያቆየውን በቂ ነጥቦች እነደሰበሰበ ይሰማኛል።
ብራይተን ስድስተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ ትልቅ ዕድል አለው።
ዳኒ ዌልቤክ ጎል አስቆጥሮ ቡድኑ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።
ግምት፡ 1 - 2
አርሰናል ከ ፉልሃም

መድፈኞቹ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ከሚያደርጉት የሻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ በፊት ፊታቸውን ወደ ሊጉ ያዞራሉ።
አርሰናል ጎሎችን ማስቆጠር አለመቻሉ አሳሳቢ ነው።
ፉልሃም ለአውሮፓ መድረክ በመፎካከር ላይ ቢሆንም የአርሰናል ተከላካይ መስመር ጥንካሬ ለድል ያበቃቸዋል።
ግምት፡ 2 - 0
ዎልቭስ ከ ሰንደርላንድ
ሰንደርላንድ ባለፈው ሳምንት በፎረስት ከደረሰበት የሚያገግምበት ጨዋታ እንደሚሆን እገምታለሁ።
ዎልቭስ በውድድሩ ዓመቱ ደካማ ሆኖ አሳልፏል።
ይህንን ጨዋታ የሚያደርጉት በሦስት ጨዋታዎች ተሸንፈው ብቻ ሳይሆን እንድም ጎል ሳያስቆጥሩ ነው።
ግምት፡ 0 - 1
እሑድ
በርንመዝ ከ ክሪስታል ፓላስ
በርንመዝ ባለፉት 14 ጨዋታዎች ያልተሸነፉ ሲሆን ዘንድሮ በሜዳቸው የተሸነፉት ሁለት ጊዜ ብቻ ነው።
ፓላስ በዩሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ከሻክታር ዶኔስክ ጋር ላለበት የመልስ ጨዋታ በሚያስበበት ጊዜ የሚደረግ መሆኑ በርንመዝን ይጠቅማል።
ጨዋታው ተንካራ ፉክክር ቢደረግብትም ባለሜዳዎቹ እንደሚያሸንፉ እገምታለሁ።
ግምት፡ 2 - 1
ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል

ከሁለቱ አሰልጣኞች ዕጣ ፈንታ ውጭ ብዙዎች ከቀድሞው በተቃራኒ ስለዚህ ጨዋታ ብዙም ትኩረት አልሰጡትም።
ይህንን ጨዋታ ለመገመት በጣም ይከብዳል።
ሊቨርፑል በድንቅ አቋም ላይ የሚገኘውን ቡርኖ ፈርናንዴዝን ማቆም ይኖርበታል።
ሞሐመድ ሳላህ በዚህ ጨዋታ ላይ አይሰለፍም።
ግምት፡ 2 - 2
አስቶን ቪላ ከ ቶተንሃም
ቶተንሃም በሊጉ ለመቆየት ከቀሪዎቹ አራት ጨዋታዎች ሦስቱን ማሸነፍ ይጠበቅበታል።
ቡድኑ ከወራት በኋላ የመጀመሪያ ድሉን ከሊጉ በወረደው ዎልቭስ ላይ አስመዝግቧል።
ቪላ በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ከፎረስት ጋር ላለበት ጨዋታ ትኩረት ማድረጉ ለስፐርስ ይጠቅመዋል።
ሆኖም ጨዋታውን ቪላ አሸንፎ ስፐርስ ላይ ጫናው እንደሚበረታ እገምታለሁ።
ግምት፡ 2 - 0
ሰኞ
ቼልሲ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት
በዚህ ጨዋታ የትኛውን ቼልሲ እንመለከታለን?
ቡድኑ በኤፍኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜ ሊድስ ሲያሸንፍ ጥሩ ቢንቀሳቀስም ከብራይተን ጋር የነበረው ቡድን ግን ደካማ ነበር።
ፎረስት በበኩሉ በጥሩ አቋም ላይ መሆኑን እያሳየ ነው።
ቡድኑ በአውሮፓ መድረክ ጨዋታ ቢኖርበትም ክሪስ ዉድ ጎል አስቆትሮ ነጥብ እንደሚጋሩ እገምታለሁ።
ግምት፡ 1 - 1
ኤቨርተን ከ ማንቸስተር ሲቲ
ሲቲ ባለፉት ስድስት ጨዋታዎች አሸንፎ ነው ወደዚህ ጨዋታ የሚመጣው።
ኤቨርተን በሜዳው ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን ሲቲን እንደሚፈትን እገምታለሁ።
ኤቨርተን አንድ ነጥብ ሊያገኝ ቢችልም ኧርሊንግ ሃላንድ፣ ራያን ሸርኪ፣ ዠርሚን ዶኩ እና አንቶኒ ሴሜንዮን የያዘው የሲቲ የአጥቂ መስመር የማሸነፊያ ጎሎችን እንደሚያስቆጥሩ አስባለሁ።
ግምት፡ 1 - 2














