BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
ቀጥታ, በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራ የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን አዲስ አበባ ገባ
በመጪው ሰኞ ሰባተኛውን አጠቃላይ ምርጫን የሚታዘቡ የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች አዲስ አበባ መግባታቸውን ኅብረቱ አስታወቀ። በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራው የኅብረቱ ታዛቢዎች ከ37 አገራት የተውጣጡ እና 73 አባላትን የያዘ መሆኑን በመግለጫው ላይ ተገልጿል።
በአማራ ክልል ከሚገኙ 138 የምርጫ ክልሎች በስምንቱ ምርጫ እንደማይደረግ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ
በመላ አገሪቱ ሰኞ ግንቦት 24 በሚደረገው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በአማራ ክልል ከሚገኙ 138 የምርጫ ክልሎች መካከል በስምንቱ ምርጫ እንደማይደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ቦርዱ በተጨማሪም የዘንድሮው አገራዊ ምርጫ በትግራይ ክልል ከሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ጋር በአንድ ላይ ምርጫ የማይካሄድ መሆኑን ገልጿል።
ከፖለቲካዊ ፍጥጫ እስከ ወታደራዊ እርምጃ - በትግራይ ክልል ሊፈጠሩ የሚችሉ አራት ቢሆኖች
ህወሓት፤ ፌደራል መንግሥት ሕገ ወጥ ባለው ምርጫ የተቋቋመውን የትግራይ ክልል መንግሥት መመለሱን ተከትሎ የፕሪቶሪያ ስምምነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አደጋ ውስጥ የገባ ይመስላል። የክልሉ ሁኔታው አሁን ባለበት ይቀጥላል ወይስ ፌደራል መንግሥት እርምጃ ይወስዳል? ሥልጣን የተቆጣጠረው ህወሓትስ ወደ ወታደራዊ እርምጃ ይገባ ይሆን? ወይስ ሁለቱ አካላት አንዳች ስምምነት ላይ ይደርሳሉ?
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ - 2018
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አገራዊ ምክክር እየተደረገ ያለው የአገሪቱን መሪ የሥልጣን ዘመን "ለመገደብ" መሆኑን ተናገሩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አገራዊ ምክክር እየተደረገ ያለው በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ያለ ማብቂያ የተጠቀመጠውን የአገሪቱን መሪ የሥልጣን ዘመን "ለመገደብ" መሆኑን ተናገሩ። መንግሥት "ሥልጣኑ በሕግ ተገድቦ" ሕገ መንግሥት እንዲሻሻል እየጠየቀ ባለበት ሁኔታ በአገራዊ ምክክሩ "አንወያይም" ያሉ አካላትን ተችተዋል።
ብልጽግና ፓርቲ፤ የአብን እና የኢዜማ አመራሮች በሚወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች ዕጩ አላቀረበም
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ባላቀረበባቸው ከ80 በላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ውስጥ የተቃዋሚዎቹ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አመራሮች የሚወዳደሩባቸው የምርጫ ክልሎች እንደሚገኙ ቢቢሲ ተገንዝቧል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መራጮች እንዲመዘገቡ የተለያዩ ጫናዎች እየተደረጉ መሆናቸውን ገለጸ
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በመራጮች የምዝገባ ሂደት ወቅት "ቤት ለቤት በመሄድ" ካርድ ውሰዱ ከሚል አንስቶ "ማኅበራዊ አገልግሎት ማግኘት" እንዲሁም "ከደሞዝ መቁረጥ ጋር በማያያዝ" በዜጎች ላይ ተጽዕኖ እስከማድረስ ያሉተግባራትን ማስተዋሉን ገለጸ።
ብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ባላቀረበበት ትግራይ ክልል ምርጫ ይካሄዳል?
ብልጽግና ፓርቲ፤ ምርጫ የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ በሆነበት ትግራይ ክልል ለሚገኙ የፓርላማ እና የክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች አንድም ዕጩ አለማቅረቡን ቢቢቢ የተመለከተው የዕጩዎች ዝርዝር ያሳያል። ስድስት ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሁለት ቅንጅቶች በበኩላቸው 101 ዕጩዎችን አስመዝግበዋል።
ባለፈው ምርጫ ብልጽግናን ከወከሉ የአዲስ አበባ ተመራጮች ውስጥ ከ60 በመቶ በላዩ በአዲስ ተተኩ
ብልጽግና ፓርቲ ግንቦት ላይ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ለአዲስ አበባ ከተማ ካቀረባቸው 154 ዕጩዎች ውስጥ 96 ያህሉ በባለፈው ምርጫ በመዲናዋ ያልተወዳደሩ እንደሆኑ ቢቢሲ ያደረገው ዳሰሳ ያሳያል። በመጪው ምርጫ በአዲስ አበባ ዕጩ ሆነው ካልቀረቡት ተመራጮች መካከል ምክትል ከንቲባው ጃንጥራር አባይ ይገኙበታል።
ከፍተኛ ውዝግብ ስላስነሳው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ማን ምን አለ?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካካል "አከራካሪ ሆነው የቆዩ" የተባሉትን አምስት የምርጫ ክልሎች በተመለከተ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ደርሶኛል ያለውን ውሳኔ ይፋ ካደረገ በኋላ የሁለቱ ክልሎች የፖለቲካ ተዋንያን በየፊናቸው መግለጫዎችን አውጥተዋል። በትግራይ በኩል ጊዜያዊ አስተዳደሩን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ፤ በአማራ በኩል የሚገኙት ደግሞ ለውሳኔው ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
በምርጫ ለመሳተፍ በቅድመ ሁኔታ እና ሕጋዊነትን በማጣት መካከል የተወጠሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች
አስር ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ በዚህ ዓመት የሚካሄደው ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ እንዲሆን እና "ከአጃቢነት ያለፈ ተሳትፎ" እንዲኖራቸው የሚጠይቅ ቅድመ ሁኔታዎችን አቀረቡ። ራሳቸውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች አንድነት መድረክ (መድረክ) ሲሉ የሚጠሩት 10 የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ ኅዳር 3/2018 ዓ.ም. በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ "ሕጋዊነትን ለመላበስ የሚደረጉ የፖለቲካ ትወናዎች" ሲሉ ከዚህ ቀደም የተደረጉ ምርጫዎችን በመኮነን፤ ምርጫዎቹ "ነፃ፣ ፍትሃዊ እና አሳታፊ፤ በውጤታቸውም ተዓማኒ እና በሕዝብ ተቀባይነት አላገኙም" ሲሉ ተችተዋል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, የኢትዮጵያ እና የሱዳን መካሰስ እና ፍጥጫ
ለረጅም ጊዜ ወዳጅ ሆነው የቆዩት ጎረቤታሞቹ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ግንኙነታቸው ሻክሯል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በይፋ በመውጣት ከመካሰስ አልፈው ወደ ግጭት የሚያመሩ ዛቻዎች እየተሰሙ ነው። ለመሆኑ ሁለቱ ጎረቤታሞችን እዚህ ያደረሳቸው ምንድን ነው?
ቪዲዮ, ከነዳጅ ጋር አብረው ስለሚነሱ ቁልፍ ነገሮች ምን ያህል ያውቃሉ?
ለዓለም የነዳጅ እና ኃይል አቅርቦት መሠረት የሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት የአገራትን ምጣኔ ሃብት ወዳልተጠበቀ ቀውስ እየወሰደው ይገኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተደጋግሞ የሚነሳው ድፍድፍ ነዳጅ ምንድን ነው? የብሬንት ነዳጅስ? ዝርዝር መረጃው በዚህ ቪዲዮ እንመለከታለን።
ቪዲዮ, የደብረ ጽዮን በፕሬዝዳንትነት መሰየም ትግራይን ወዴት ይወስዳታል?
በትግራይ ሁለት ፕሬዝዳንቶች ተሹመዋል። ህወሓት የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት መፍረሱን በመጥቀስ ከጦርነት በፊት የነበረውን አስተዳደር መመለሱን አስታውቋል። ሌ/ጄኔራል ታደሰ በሥልጣን ላይ እያሉ ነው ደብረጽዮን ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት። ክልሉ እንዴት እዚህ ሁኔታ ላይ ደረሰ? የሌ/ጄነራል ታደሰ ዕጣ ፈንታስ ምን ሊሆን ይችላል?
ቪዲዮ, ቃላት እየተወራወሩ ያሉት ቱርክ እና እስራኤል ወደ ወታደራዊ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ?
ባለፉት ሦስት ዓመታት ቱርክ እና እስራኤል መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመፍጠር ወደ ቀጥተኛ ወታደራዊ ግጭት እያመራ መሆኑ እየተነገረ ነው። በሁለቱ አገራት መሪዎች መካከል የቃላት ጦርነቱ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ወታደራዊ ግጭት የመከሰት ዕድል ይኖራል ወይ የሚል ጥያቄን እያስነሳ ነው። የሁለቱ አገራት ውዝግብ ወዴት ያመራ ይሆን?
ቪዲዮ, ለሦስተኛ ጊዜ የመግደል ሙከራ የተደረገባቸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት
ቅዳሜ ምሽት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በርካታ የአሜሪካ ባለሥልጣናት በተገኙበት የእራት ግብዣ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረ ግለሰብ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውሏል። ትራምፕን ለመግደል የሚደረግ ሙከራ አዲስ አይደለም። እስካሁን በፕሬዝዳንቱ ላይ የተቃጡት የመግደል ሙከራዎች ምን ይመስላሉ?
ቪዲዮ, የአሜሪካ እና የኢራን ተኩስ አቁም ስምምነት
ኢራን እና አሜሪካ የሆርሙዝ ወሽመጥ ተከፍቶ መርከቦች እንዲያልፉ የሚያስችል የሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምተዋል። አገራቱን ሲያሸማግሉ የነበሩት የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሻሪፍ የተኩስ አቁሙ ወዲያውኑ ገቢራዊ እንደሆነ አስታውቀዋል። ሁለቱ አገራት እዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ወሳኙን የባሕር መተላለፊያ ማክሰኞ ሌሊት ድረስ የማትከፍት ከሆነ “ሙሉ ሥልጣኔዋ ይወድማል” የሚል ዛቻ ካሰሙ ከሰዓታት በኋላ ነው። ለመሆኑ ስምምነቱ ለሁለቱ አገራት ምን ማለት ይሆን?
አነጋጋሪ ጉዳይ
ግብፅ "ከበባ እና ትንኮሳ በሚመስል መልኩ" እየተንቀሳቀሰች ነው ስትል ኢትዮጵያ ከሰሰች
ኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት አጀንዳዋን ይፋ ካደረገች በኋላ ግብፅ "ከበባ በሚመስል መልኩ" እየተንቀሳቀሰች ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናገሩ። አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ሐሙስ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም. ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄዋን ካነሳች በኋላ ከግብፅ በኩል "ውጥረት፣ ትንኮሳ የሚመስሉ ነገሮች እየታዩ" መሆናቸውን ተናግረዋል።
'ቤተሰቦቼ ከሞትኩ በኋላ መርዶ ቢነገራቸው ይሻላል' - በሳዑዲ እስር ቤቶች የሞት ቅጣት የሚጠባበቁት ኢትዮጵያውያን
በሳዑዲ አረቢያ ሦስት ኢትዮጵያውያን ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር በተያያዘ ክስ የሞት ፍርድ ሲፈጸምባቸው ቢያንስ 65 የሚሆኑት ደግሞ ፍርዳቸው ተፈጻሚ የሚሆንበትን ጊዜ እየተጠባበቁ መሆኑን ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል። የሳዑዲ መገናኛ ብዙኃን በካሃሚስ ሙሻይት ማረሚያ ቤት የሚገኙ ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያን የሞት ፍርድ እየጠበቁ መሆኑን ዘግበዋል። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው እነዚህ ወጣቶች ከመርፈዱ በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት ይድረስልን ሲሉ ይማጸናሉ።
የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ አነሳ
የአውሮፓ ኅብረት ከሁለት ዓመት በፊት በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ ማንሳቱን አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ በአውሮፓ የሚኖሩ ዜጎቹን ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ ነው በሚል በኢትዮጵያውያን ላይ የቪዛ ገደብ ተጥሎ ቆይቷል። የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫ፤ በኅብረቱ አባል አገራት ውስጥ በሕገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በመለየት እና ወደ አገራቸው በመመለስ ረገድ መሻሻሎች ስለታዩ ገደቡ እንዲነሳ ተወስኗል።
ቻይና እና ሩሲያ ለምን 'የቅርብ ወዳጆች' ሆኑ?
ቻይና በዓለም ምጣኔ ሃብት ላይ ካላት ጉልህ ሚና እና ከፍተኛ ተጽእኖ የተነሳ ኃያላን አገራት ከቻይና ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር እየጣሩ ነው። አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት እና ሩሲያ በተለይ በዚህ ወቅት ቻይናን አጥብቀው እየፈለጓት ነው። ባለፈው ሳምንት ፕሬዝዳንት ትራምፕን ያስተናገደችው ቻይና አሁን ደግሞ ፕሬዝዳንት ፑቲንን ተቀብላለች። ከአሜሪካ እና ከሩሲያ ለቻይና ማን የቀረበ ነው?
ግብፅ እና ኤርትራ የቀይ ባሕር ጉዳይ የሚመለከተው "የጠረፉን አገራት ብቻ ነው" አሉ
ቀይ ባሕር ላይ የሚደረግ የትራንስፖርት እንቅስቃሴን እና የወደብ ትስስርን የተመለከተ ስምምነት የተፈራረሙት ግብፅ እና ኤርትራ፤ የቀይ ባሕር ጉዳይ የሚመለከተው "የቀይ ባሕር ጠረፍ አገራትን ብቻ" እንደሆነ ገለጹ። ቀይ ባሕርን ከሚያዋስኑ የባሕር ዳርቻ አገራት "ብሔራዊ ደኅንነት ጋር ቀጥተኛ ትስስር" እንዳለው በመጥቀስም "የቀይ ባሕር አጎራባች ያልሆነ አካል ቀይ ባሕርን በሚመለከቱ ጉዳዮች መግባት የለበትም" ማለታቸውም ተዘግቧል።
"ሙስሊም ነኝ፤ እንዳትተኩሱብኝ": ከሆርሙዝ መዘጋት ቀጥሎ በሶማሊያ ያገረሸው የባሕር ላይ ውንብድና
በባሕረ ሰላጤው በኢራን ላይ ጦርነት ከተከፈተ በኋላ ዋነኛው የነዳጅ መተለላፊያ የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋሩ በኃይል አቅርቦት ላይ ቀውስ ተፈጥሯል። ይህንን ተከትሎ ደግሞ ጋብ ብሎ የነበረው የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎች በመርከቦች ላይ የሚፈጽሙት ዕገታ አገርሽቷል። ይህም በሌላኛው የባሕር መተላለፊያ ቀይ ባሕር መግቢያ ላይ እየተከሰተ ያለው የባሕር ላይ ውንብድና ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል።
የአሜሪካ የኤርትራን ማዕቀቦች ማንሳት፡ ቀይ ባሕር የሸፈነው የሰብአዊ መብት ጥያቄ?
አሜሪካ የኤርትራን ማዕቀቦች ለማንሳት ማቀዷ ሲሰማ ከጀርባ ያለው ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ምክንያት ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ አጭሯል። ኤርትራ ላይ የሚቀርቡ የሰብአዊ መብት ጥሰት ክሶችን በተመለከተ ተጠያቂነት እና ፍትሕ ሳይሰፍን ማዕቀቦችን ማንሳት ምን ያስከትላል? ለምን አሁን ማዕቀቦችን ማንሳት አስፈለገ? ይህ የአሜሪካ ሐሳብ ለኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ምን ማለት ነው? የሚሉ ጥያቄዎችም እየተነሱ ነው።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የሥልጣን ዘመናቸው ማብቃቱን ተከትሎ የተፈጠረው አጣብቂኝ
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ያደረጉትን ሙከራ ተከትሎ ከዚህ ቀደም አጋጥሟቸው አያውቅም የተባለ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተጋፈጡ ነው። በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት የፕሬዝዳንቱ የሥልጣን ዘመን የሚያበቃው አርብ ግንቦት 7/2018 ዓ.ም. ነው። ይህ ሁኔታም ሶማሊያን ቀውስ ውስጥ በማስገባት ለአልሻባብ በር ሊከፍት ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
እናት እና ልጅን ጨምሮ ከ30 በላይ ሰዎች የተገደሉበት የመተከል ጥቃት እና ያሳደረው ስጋት
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማክሰኞ ግንቦት 4/2018 ዓ.ም. በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ከ30 ሰዎች በላይ መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። ይህ በርካታ ሰዎች የተገደሉበት እና ጉዳት የደረሰባቸው ጥቃት የተፈጸመው ከክልሉ ዋና ከተማ አሶሳ መንገደኞችን ባሳፈሩ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ ነው።
አሜሪካ በኤርትራ ላይ ጥላቸው የቆዩ ማዕቀቦች የትኞቹ ናቸው? በተለይ እነማንን ይመለከታሉ?
አሜሪካ በኤርትራ ላይ የጣለቻቸውን ማዕቀቦች ለማንሳት እና ከአሥመራ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ማቀዷ ተዘግቧል። ኤርትራ በኢትዮጵያ ትግራይ ውስጥ በተካሄደው ጦርነት ውስጥ ከነበራት ተሳትፎ ጋር በተያያዘ በአሜሪካ ማዕቀብ ተጥሎባታል። ለመሆኑ አሜሪካ በኤርትራ ላይ የጣለቻቸው ማዕቀቦች የትኞቹ ናቸው?
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት
በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የአሜሪካንን ባሕር ኃይል እየፈተኑ ያሉት የኢራን ትናንሽ ጀልባዎች
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን ባሕር ኃይል እንዳወደሙ ቢናገሩም፣ ኢራን ትናንሽ ፈጣን ጀልባዎችን በመጠቀም በሆርሙዝ ወሽመጥ የመርከቦችን እንቅስቃሴን መግታት ችላለች። ስለእነዚህ ውጤታማ የኢራን ፈጣን ወታደራዊ ጀልባዎች ምን እናውያለን?
አሜሪካ እና ኢራን ድል እንደተቀዳጁ እያወጁ ባሉበት ጦርነት አሸናፊው ማን ነው?
አሜሪካ ከኢራን ጋር የምታደርገውን ጦርነት ማቆሟን እየተናገረች ነው። በሁለቱ አገራት መካከል የተኩስ አቁም ከተደረገ ከሳምንታት በኋላ ማክሰኞ ዕለት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ "ኢፒክ ፊውሪ' በማለት የተጠራው ዘመቻ ማብቃቱን ተናግረዋል።በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በተደረገው ጦርነት ማን አሸነፈ?
መሪዎቹ እየተገደሉበት ባለበት ጸንቶ የቀጠለው የኢራን የጦርነት ወቅት አመራር የተዋቀረው እንዴት ነው?
ኢራን በአሜሪካ እና በእስራኤል እየተፈጸመባት ባለው ጥቃት ከጠቅላይ መሪዋ ከአያቶላህ አሊ ኻሜኒ ጀምሮ በርካታ ቁልፍ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ መሪዎቿ ተገድለውባታል። ነገር ግን አመራሯ ሳይፈረካከስ እየተተካካ ፍልሚያውን ቀጥሏል። ለመሆኑ የኢራን አመራር በዚህ ጦርነት ውስጥ ባለበት ጸንቶ እንዴት ሊቀጥል ቻለ?
የሚሳዔል ዒላማ የሆኑት ቅንጡ ከተሞች፡ የኢራን ጦርነት በባሕረ ሰላጤው አገራት ውስጥ ምን ለውጥ ያስከትላል?
የቅንጦት እና የንግድ መናኸሪያዎች ሆነው የቆዩት የባሕረ ሰላጤው አገራት ቅንጡ ከተሞች በኢራን ላይ የተከፈተውን ጦርነት ተከትሎ ገጽታቸው እየተቀየረ ነው። አገራቱ በጦርነቱ ዳር ላይ የቆሙ ቢሆንም በየዕለቱ የኢራን ሚሳዔሎች እየጎበኟቸው ነው። ይህ ጦርነት በወደፊት ገጽታቸው ላይ ምን ውጤት ይኖረዋል?
ኢራን በመካከለኛው ምሥራቅ ፍርሃት የፈጠረችበት ርካሹ ድሮን
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መክፈታቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ጦርነት እየተካሄደ ነው። ኢራን እየተፈጸመባት ላለው ጥቃት አጸፋውን በቀጣናው ባሉ የአሜሪካ ወዳጅ አገራት ላይ እየፈጸመች ነው። ለዚህ ደግሞ ኢራን ርካሽ እና ውጤታማ የሆኑትን ሻሂድ-136 የተባሉ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን በስፋት እየተጠቀመች ነው። ይህ በምሥል እና በቪዲዮ የተደገፈው ዘገባ ስለድሮኖቹ ምንነት ይተነትናል።
ከየፈርጁ
ኢትዮጵያ ለምን እስካሁን 'በጅብ ሃብቷ' አልተጠቀመችም?
በተለምዶ የጅቦች ስም የሚነሳው ከክፉ ነገር ጋር ተያይዞ ነው። ጅቦችን ማጉረስ ባህል ከሆነበት የኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ክፍል ውጭ ስለ ጅቦች ያለው አመለካከት ተመሳሳይ ነው ማለት ይቻላል። በመቀለ ዩኒቨርስቲ እና በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኘው የሼፊልድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ግደይ ይርጋ ግን የተለየ ዕይታ አላቸው። ጅቦች የካንበን ልቀትን ይቀንሳሉ፤ አካባቢን በማጽዳት ከበሽታ ይከላከላሉ፤ ገንዘብም ይቆጥባሉ ቢባል ብዙዎች ያምኑ ይሆን?
'የማያመልጡት ወጥመድ'፡ እናት በመሆናቸው የሚጸጸቱት ሴቶች
. . . "እናትነት ባንፈልገው እንኳ የሚከተለን እና የምናከናውነው ማለቂያ የሌለው ሥራ ነው፣ ምክንያቱም ልጆቻችን በእኛ ላይ ጥገኛ ናቸው… የማናመልጠው ወጥመድ ይመስላል" ትላለች። እናት መሆን ምን ያህል "አስከፊ" እንደሆነም ያለማመንታት ትናገራለች። ስለልጇ ስትጠየቅ ግን ድምጸቷ ጭምር ብሩህ ይሆናል።
ሐረር ውስጥ ለ12 ዓመታት ለመውለድ የሞከረች እናት በአንድ ጊዜ አምስት ሕፃናትን ተገላገለች
ለ12 ዓመታት ልጅ ለመውለድ የሞከረች የሐረሪ ክልል ነዋሪ በአንድ ጊዜ አምስት ልጆችን መገላገሏ ተገለጸ። በድሪያ አደም የተባለችው እናት እሷና ባለቤቷ "በአንድ ጊዜ አምስት ልጆች ስላገኙ እጅግ እንደተደሰቱ" ተናግራለች።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አጃኢብ!
አባቱን ገድሎ 12 ዓመት የተፈረደበት ልጅ ይቅርታ እንዲደረግለት የሚጠይቀው ቤተሰብ
የ27 ዓመቷ ሳራ ከእንባዋን ጋር እየታገለች ለግድያው ምክንያት የሆነውን አሳዛኝ ክስተት ለቢቢሲ ተናግራለች። ካርሎስ ለዓመታት ሞይሰስን እንደደበደበና አካላዊ ጥቃት እንደፈጸመበት የሰማችው ያኔ ነበር።
በአፍሪካ የፊልም አዋርድ ላይ የታየው ከ500 ዳቦዎች የተሰራው ቀሚስ
እሁድ ግንቦት 2 2018 ዓ.ም. በናይጄሪያ በተካሄደው 12ኛው የአፍሪካ ፊልሞች አዋርድ ላይ ታዋቂ ሰዎች፣ የፊልም ባለሙያዎች እንዲሁም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በተለያዩ አልባሳት ተውበው ተገኝተዋል። በዕለቱ ከተገኙት ስመ ጥር ሰዎች ሁሉ ግን የአንዷ ታዋቂ የቴሌቪዥን ተዋናይ አልባሳት የበለጠ መነጋገሪያ ሆኖ አምሽቷል።
የተመለሱ ጥያቄዎች
ያለባቸው የጤና ችግር ሕክምና እንዲያጠኑ ያደረጋቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች
በረከት በቀለ፣ ኪምቢፊዳ በሚል ስም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይታወቃል። ወደ ቲክቶክ ብቅ ከማለቱ አስቀድሞ "በስፓይና ቢፊዳ (spina befida) የተያዝኩ ብቸኛው ሰው እኔ ብቻ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር" ይላል። የአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት መሥራቹ ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬም ልክ እንደ በረከት ሁሉ ከስፓይና ቢፊዳ (የነርቭ ዘንግ ክፍተት) ጋር ነው የተወለደው። አሁን 33 ዓመት እንደሆነው የሚናገረው ዶ/ር ነቢያት፣ በተወለደ በ22ኛው ቀን የስፓይና ቢፊዳ የቀዶ ሕክምና ተደርጎለታል። ሁለቱም ወጣቶች ከራሳቸው ህመም ተነስተው ሕክምና ለማጥናት መወሰናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያዊ እና ኬንያዊ አትሌቶች ማራቶንን ከሁለት ሰዓት ባነሰ ጊዜ እንዲጨርሱ ያስቻላቸው ምስጢር ምንድን ነው?
ትናንት እሁድ በለንደን የተካሄደው የማራቶን ውድድር ኬንያዊው ሳባስቲያን ሳዌ እና ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጄልቻ ከሁለት ሰዓት በታች ተከታትለው በመግባት ዓለምን አስደምመዋል።
አስፈላጊ ነገር ግን ጎጂ የሆነውን የጨው አወሳሰዳችንን እንዴት መመጠን እንችላለን?
ጨው ምግባችንን የበለጠ ያጣፍጠዋል። ለሰው ልጅ ሕይወትም አስፈላጊ ነው። በጨው ውስጥ የሚገኘው ሶዲየም በሰውነት ውስጥ የሚኖረውን ትክክለኛውን የውሃ መጠን ለመጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው። ህዋሳትም ንጥረ ምግቦችን እንዲወስዱ ይረዳል። በምግብ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው የቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ፕሮግራም “ዘ ፉድ ቼይን” ጨው በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ወሳኝ ሚና እና ለአንድ ሰው ከመጠን በላይ የሚባለው የጨው ፍጆታ ምን ያህል ነው የሚለውን ተመልክቷል።
ከሆርሙዝ በፊት ዓለም ላይ ምን ያህል የባሕር እንቅስቃሴ እገዳዎች ተጥለዋል? ምን ያህል ውጤታማ ነበሩ?
አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡ እና የሚወጡ መርከቦች ላይ እገዳ መጣሏ ጥንታዊ የወታደራዊ ጫና መፍጠሪያ ስልትን መልሶ ያመጣ ነው። ይህ እርምጃ የባሕር መስመሮችን በመዝጋት ምጣኔ ኃብታዊ ጫና መፍጠር፣ ንግድን ማስተጓጎል እና ተገዳዳሪው አካል አቋሙን እንዲቀይር ወይም እጅ እንዲሰጥ የማስገደጃ ስልት ነው። ታሪክ የሚያሳየን እንዲህ ዓይነት ስልቶች ጫና በመፍጠር ረገድ ውጤታማ ቢሆኑም ሰፊ ተጽዕኗቸው ግን ከሚታሰበው በላይ ውስብስብ መሆኑን ነው።











































































































