ኦፕንኤአይ 90 ዓመት ላስቆጠረ ከባድ የሒሳብ ጥያቄ በ88 ሰዓታት ውስጥ መልስ ማግኘቱን አስታወቀ

የፎቶው ባለመብት, Reuters
ኦፕንኤአይ 90 ዓመት ላስቆጠረ ከባድ የሒሳብ ጥያቄ በሰዓታት ውስጥ ምላሽ ማግኘቱን አስታወቀ።
የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሞዴል እና በሺህዎች የሚቆጠሩ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቦቶችን በመጠቀም ለሒሳብ ጥያቄው በ88 ሰዓታት ውስጥ መልስ ማግኘት ተችሏል።
ቻትጂፒቲን የሠራው ኦፕንኤአይ ትናንት ማክሰኞ እንዳስታወቀው 10,000 የኤአይ ቦቶች በመጠቀም የሒሳብ ችግሩ ተፈትቷል።
የሒሳብ ጥያቄው 'ናቪየር-ስትሮክስ ኢኩዌዥንስ' የተባለው የሒሳብ ቀመር ክፍል ሲሆን፤ ለ90 ዓመታት ያህል ስሌቱ ሳይረጋገጥ ቆይቷል።
ኦፕንኤአይ ለዚህ የሒሳብ ጥያቄ ያገኘውን መፍትሔ "ወሳኝ ምዕራፍ" ብሎታል። ሰው ሠራሽ አስተውሎት በፍጥነት እየተሻሻለ መምጣቱን እንደሚያሳይም ገልጿል።
ኦፕንኤአይ ያገኘው መልስ በገለልተኛ ወገን ገና አልተረጋገጠም።
የአሜሪካው የሒሳብ ጥናት ተቋም 'ክሌይ ማቲማቲክስ' የሒሳብ ችግሮችን ለሚፈቱ የመጀመሪያ ሰዎች የገንዘብ ሽልማት ይሰጣል።
በሒሳብ ውስጥ ታዋቂ ለሆኑ ሰባት ከባድ የሒሳብ ችግሮች (ሚሊኒየም ፕራይዝ ፕሮብለምስ) መፍትሔ ላገኙ ሰዎች ነው ሽልማቱ የሚሰጠው።
ነሐሴ መጨረሻ ላይም የሒሳብ ቀመር የሚሠራ የኤአይ ሞዴል ማሠልጠን መጀመሩን አስታውቋል።
የኤአይ ሞዴል በከፍተኛ የመረጃ ስብስብ የሚሠለጥን ሲሆን፤ መረጃ አብላልቶ የወደፊት ውጤትን ያመላክታል።
ኦፕንኤአይ በሒሳብ ቀመር ላይ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሞዴሉን ለመጠቀም ወስኗል።
ኦፕንኤአይ እንዳለው ከሚሊኒየም ፕራይዝ የሒሳብ ችግሮች መካከል ለሁለቱ መፍትሔ መገኘቱን ጭምጭምታ ሰምቷል።
በሺህዎች የሚቆጠሩ የኤአይ ቦቶችን በመጠቀም የተቀሩትን ችግሮች ለመፍታትም ዕቅድ አውጥቷል።
በአውሮፓውያኑ መስከረም 5፣ ናቪየር-ስትሮክስ ኤግዚስታንስ እና ስሙዝነስ ለተባሉት የሒሳብ ችግሮች በ88 ሰዓታት መፍትሔ ማግኘቱን ይፋ አድርጓል።
በሺህዎች የሚቆጠሩት የኤአይ ቦቶች በአጭር ጊዜ መፍትሔውን አግኝተዋል። ቦቶቹ ወደ 3 ቢሊዮን ገደማ መልዕክት መለዋወጣቸው ተገልጿል። ለናቪየር-ስትሮክስ የሒሳብ ችግር ብቻ 130 ቢሊዮን የሚጠጉ መረጃዎች ሰጥተዋል።
ኦፕንኤአይ ባወጣው መረጃ መሠረት ይሄንን ሥራ ለማከናወን 10 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል።
ከአራቱ የሚሊኒየም ፕራይዝ የሒሳብ ጥያቄዎች መካከል ኦፕንኤአይ ሁለቱን መመለሱን አስታውቋል።
ለጥያቄዎቹ ምላሽ ያገኘ አንድ ሚሊዮን ዶላር ይሸለማል።
ኦፕንኤአይ ባወጣው መግለጫ "ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ማግኘታችንን ይፋ ያደረግነው ኤአይ የደረሰበትን ልህቀት ለማሳየት ነው። ለውጤታችን የሚሊኒየም ሽልማትን የመውሰድ ዕቅድ የለንም" ብሏል።
ኦፕንኤአይ ለሒሳብ ችግሮቹ መፍትሔ አግኝቻለሁ ማለቱ ውዝግብ አስነስቷል።
በኒው ዮርክ ዩኒቨርስቲ የሒሳብ ምሁር ትሪስተን በክማስተር እንደተናገሩት ሌቪት አልፖግ ከተባሉ ሌላ የሒሳብ ምሁር ጋር እነዚህን የሒሳብ ጥያቄዎች ለመመለስ እየሠሩ ይገኛሉ።
ሌቪት የሚሠሩት የኦፕንኤአይ ተገዳዳሪ ለሆነው አንትሮፒክ ነው።
ባለሙያዎቹ የኦፕንኤአይን ኮዴክስ በመጠቀም መፍትሔ ለማግኘት መሥራታቸውን ቀጥለዋል።
ኦፕንኤአይ ለሒሳብ ጥያቄዎቹ መልስ ለማግኘት መመራመር የጀመረው ባለሙያዎቹ ችግሩን ለመፍታት እየሞከሩ እንደሆነ ከተሰማ በኋላ መሆኑን ትሪስተን ተናግረዋል።
የኦፕንኤአይን የሒሳብ ስሌት እንዳልተመለከቱት ባለሙያው ተናግረዋል። ኦፕንኤአይ በበኩሉ የባለሙያዎቹን ምርምር እንዳላየው ገልጿል።















