አሜሪካ በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ለማለፍ ለኢራን ተጨማሪ ክፍያ የሚከፍሉ የመርከብ
ድርጅቶች ማዕቀብ እንደሚጣልባቸው አስጠነቀቀች።
አርብ ዕለት በአሜሪካ የውጭ አገራት ንብረት ላይ ቁጥጥር የሚያደርገው ቢሮ ባወጣው
ማስጠንቀቂያ አሜሪካውያን ግለሰቦችም ሆኑ ኩባንያዎች ለኢራን የመንግሥት ተቋማት ምንም ዓይነት ቀረጥ እንዳይከፍሉ አግዷል።
አሜሪካዊ ያልሆኑ ግለሰቦች እና ኩባንያዎች ደግሞ በወሽመጡ በኩል ለማለፍ ለቴህራን
ቀረጥ የሚከፍሉ ከሆነ ማዕቀብ እንደሚጣልባቸው አስታውቋል።
የቁጥጥር መስሪያ ቤቱ “የባሕር ላይ ትራንስፖርት ኢንዱስትሪው ተሳታፊዎች ከኢራን ወደቦች ወይንም የመርከብ ድርጅቶች
ጋር የሚሰሩ እንዲሁም ወደ ኢራን ወደቦች የሚሄዱ ከሆነ ተደራራቢ ማዕቀብ
ሊጣልባቸው ይችላል” ብሏል።
ከሁለት ወር በፊት አሜሪካ እና እስራኤል በቴህራን ላይ ጦርነት ማወጃቸውን ተከትሎ
ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ዘግታለች። አሜሪካ በምትኩ ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረግ ማንኛውንም የመርከቦች እንቅስቃሴ አግዳለች፥።
ኢራን የአሜሪካን እርምጃ “የባህር ላይ ውንብድና” ስትል በመጥራት ኮንናዋለች።
ቴህራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ያለምንም እንከን ለመቅዘፍ ከሚፈልጉ መርከቦች ቀረጥ
እየሰበሰበች መሆኑን አስታውቃለች።
ባለፈው ሳምንት የኢራን ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባዔ ሃሚድሬዛ ሀጂ ባባኤ የመጀመርያው
ከቀረጥ የተሰበሰበ ገንዘብ በአገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ መቀመጡን ተናግረዋል።
ምክትል አፈ ጉባዔው ተጨማሪ ማብራሪያ ያልሰጡ ሲሆን ቀረጡ የተሰበሰበበት መንገድንም
ሆነ ማን እንደከፈለውም ከመናገር ተቆጥበዋል።
ቢቢሲ ይህንን የምክትል አፈ ጉባዔውን አስተያየት ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አልቻለም።
የአሜሪካ የውጭ ድርጅቶችን ሃብት የሚቆጣጠረው መስሪያ ቤት ያወጣው ማስጠንቀቂያ ክፍያው
በጥሬ ገንዘብ ወይንም “በዲጂታል፣
በቁሳቁስ ለውጥ፣ በስጦታ እንዲሁም ለኢራን ኢምባሲዎች በሚደረግ የበጎ አድራጎት ልግስና” ሊሆን አንደሚችል አስታውቋል።
ኤጀንሲው አሜሪካዊ ያልሆኑ ግለሰቦች ክፍያ የሚፈጽሙ ከሆነ በወንጀል እንደሚጠየቁም
ተናግሯል።
ኤጀንሲው አክሎም “የኢራን ዋና የገንዘብ ምንጮችን በተለይም ፔትሮሊየም እና ፔትሮኬሚካል
ዘርፉን ዒላማ ማድረጌን እቀጥላለሁ” ብሏል።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት አርብ ዕለት በሦስት የኢራን የሃዋላ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ
የኢራን የነዳጅ ገንዘብን ወደ ሌላ ዓለም አቀፍ ገንዘብ ይቀይራሉ በሚል ማዕቀብ ጥሏል።
የግምጃ ቤት ኃላፊው ስኮት ቤስኔት “የአገዛዙን ገንዘብ የማመንጨት፣ ፈንዶችን የማስገባት
እና ማዕቀቦችን ለማለፍ የምታደርገውን ሙከራ ዒላማ እነደሚያድጉ ተናግረዋል።
ስኮት
ቤሴንት “አገዛዙ ገንዘብ እንዳያመነጭ፣ እንዳያንቀሳቅስ እና
ወደ አገር ውስጥ እንዳያስገባ ማዐዕቀቦቸን ለማለፍ የሚያደርገውን ሙከራ ያለመታከት
ክትትል ማድረጋችንን እንቀጥላለን ብለዋል።