ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
አዳዲስ ታሪክ የሚመዘገብበት 23ኛው የዓለም ዋንጫ ውድድር ሙሉ መረጃን እዚህ ያገኛሉ
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 1 ደቂቃ
የዓለማችን ትልቁ የእግር ኳስ ውድድር የዓለም ዋንጫ በ23ኛ ዙር ውድድር በርካታ አዳዲስ ነገሮች የሚታዩበት ሆኖ ከሰኔ 4 አስከ ሐምሌ 12 ድረስ ይካሄዳል።
በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት አገራት ውስጥ የሚካሄደውን የዓለም ዋንጫ ተጎራባቾቹ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ያስተናግዱታል።
በተጨማሪም በውድድሩ ታሪክ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አገራት የሚሳተፉ ሲሆን፣ ካለፉት 22 የዓለም ዋንጫ ውድድሮች በበለጠ 48 አገራት ስለሚሳተፉ ትልቁ የዓለም ዋንጫ ውድድር ይሆናል።
ከአንድ ወር በላይ በሚቆየው ውድድር 104 ግጥሚያዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ በዚህ በየደቂቃው በሚሻሻለው ሰንጠረዥ ላይ ስለውድድሩ ሁሉንም መረጃ ያገኛሉ።
የውድድር ቦታዎች፣ ቀናት፣ ሰዓታት፣ ውጤቶች፣ የምድብ ድልድል እና ደረጃ እንዲሁም ሌሎች የጨዋታ ዝርዝር መረሃ ግበሮች እዚህ ይቀርባሉ።