ትራምፕ ከአገር ውጭ የኤኤይ የመረጃ ማዕከላትን የሚገነቡ የአሜሪካ ድርጅቶችን እንደሚያግዱ አስጠነቀቁ

የፎቶው ባለመብት, Bloomberg via Getty Images
የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከአገር ውጭ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) የመረጃ ማዕከላትን የሚገነቡ የአሜሪካ ኩባንያዎችን እንደሚያግዱ አስጠነቀቁ። ይህን በሚያደርጉ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ላይም “ ከፍተኛ ግብር እንደሚጥሉ” ዝተዋል።
“ሁሉንም ነገር እዚሁ በአገር ውስጥ ነው ማድረግ ያለብን” ያሉት ፕሬዚደንቱ፣ ሌሎች በካቢኔያቸው ውስጥ ያሉ ሰዎች ስለ ፖሊሲው ለመጀመሪያ ጊዜ እየሰሙ እንደሆነ ተናግረዋል።
ትራምፕ አስተዳደራቸው ስለወጠነው ፖሊሲ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጡም።
ጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በተካሄደው የአጋማሽ ዘመን ምርጫ የኤአይ የመረጃ ማዕከላት ጉዳይ ዋነኛ መሟገቻ የነበረ ሲሆን በርካታ የዴሞክራት እጩዎች በእነዚህ ማዕከላት ግንባታ ላይ የበለጠ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።
ሆኖም እንደ ሜታ እና ጉግል ያሉ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በውጪ አገር የመረጃ ማዕከላትን ለመገንባት ስምምነት አድርገዋል። አሁን ላይ ትራምፕ ያሉት ፖሊሲ ተፈፃሚ ከሆነ ስምምነታቸው እንዴት ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችል ግልጽ አይደለም።
ትራምፕ ከእስያ ጉዟቸው ከተመለሱ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ ኩባንያዎቻችን ከአገራችን ውጪ የመረጃ ማዕከላትን እንዲገነቡ አንፈቅድም” ብለዋል።
“ቻይና ሁሉንም ትወስድብናለች፤ ይህ እንዲሆን ደግሞ አንፈቅድም” ሲሉም ምክንያታቸውን አስረድተዋል።
ትራምፕ አሁን ላይ እያነሱት ያሉት ሃሳብ ወደ ፖሊሲነት የሚለወጥ እንደሆነ ግልጽ አይደለም።
“ይህ ሰበር ዜና ይሆን እንደሆነ አላውቅም፤ ለሕዝቦቼ እንኳን አልነገርኳቸውም፤ ነገር ግን እዚሁ መሆናቸውን [ ኩባንያዎቹ] አሁን እየነገርኳቸው ነው” ብለዋል።
ትራምፕ ስለ ፖሊሲው የተናገሩት አሜሪካ በመረጃ ማዕከል ግንባታ ላይ ግንባር ቀደም እንደሆነች እና ከኤአይ ጋር በተገናኘ ቻይና አሜሪካን እንድትበልጥ እንደማይፈልጉ ከተናገሩ በኋላ ነው።
- ተያያዥ ዘገባዎች፡













