‘የመጀመርያ ደረጃ ግኝቶች’ የሚጠቁሙት ተጠርጣሪው ‘የአስተዳደሩን ባለሥልጣናት’ ዒላማ ማድረጉን ነው- አቃቤ ሕግ
የአሜሪካ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቶድ ብላንቼ በዋይት ሐውስ ዘጋቢዎች የእራት ግብዣ ላይ ተኩስ የከፈተው ተጠርጣሪ ምርመራ እንደቀጠለ ነው አሉ።
ነገር ግን “የመጀመርያ ደረጃ” ግኝቶች ዒላማ ያደረገው የአስተዳደሩን ባለሥልጣናት እንደሆነ እና ይህም ፕሬዚዳንቱንም ሊያካትት ‘እንደሚችል’ እንደሚያሳዩ ተናግረዋል።
ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ለኤንቢሲ እንደተናገሩት መርማራዎች ተጠርጣሪው መሣሪያውን የገጣጠመው በሆቴሉ ውስጥ ነው የሚለውን እያጣሩ መሆኑን አስታውቀዋል።
አክለውም ተጠርጣሪው “ብዙም ርቀት መሄድ አልቻለም” ብለዋል።
“በጣም በትንሹ ነው ደህንነቶችን ያለፈው” ያሉት ብላንቼ ተጠርጣሪው ከሎስ አንጀለስ ወደ ቺካጎ እናም ወደ ዋሺንግተን በባቡር ተጉዞ ሊሆን ይችላል ብለዋል።
ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ተጠርጣሪው ላይ ሰኞ ክስ እንደሚመሰረት አረጋግጠዋል።
ብላንቼ ከሲቢኤስ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ወቅት ተጠርጣሪው ለመርማሪዎች ትብብር ለማድረግ ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን ተናግረዋል።