ቀጥታ, ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ መስጠት ተጀመረ

ከትግራይ ክልል በስተቀር በመላ አገሪቱ በሚካሄደው ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ድምጽ መስጠት ተጀምሯል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ እና በአማራ ክልል ደግሞ በተወሰኑ አካባቢዎች ምርጫው በዛሬው ዕለት እንደማይካሄድ ቀደም ብሎ አስታውቋል።

ጭምቅ ሃሳብ

በመላ አገሪቱ ሰባተኛው ዙር የኢትዮጵያ አገራዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው

የቀጥታ ሽፋን

  1. ከ50 ሚሊዮን በላይ መራጮች

    ለሰባተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ዛሬ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም. መራጮች በየአካባቢያቸው ድምጽ እየሰጡ ነው። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከትግራይ ክልል እና ከአንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች ውጪ ምርጫው እንደሚካሄድ አስታውቋል።

    ለዚህ ምርጫ 50.5 ሚሊዮን ሰዎች በመራጭነት የተመዘገቡ ሲሆን፣ ይህም አገሪቱ ካላት አዋቂ ሕዝብ ከሁለት ሦስተኛው የሚበልጥ ነው።

    የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ እንሚያመለክተው ለመራጭነት ከተመዘገቡት ከ50 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን መካከል ሴቶች 46 በመቶ እንዲሁም ወንዶች 54 በመቶ ናቸው።

    ዘንድሮ በመራጭነት የተመዘገቡት ዜጎች ቁጥር ከአምስት ዓመት በፊት ከተመዘገቡት በ32 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፣ ካለፉት ስድስት ምርጫዎችም የበለጠ ነው።

    ሥዕላዊ መግለጫ
  2. የሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ በምስል

    ሐመር ምርጫ ክልል፣ ቆላጃ አንጉዴ ምርጫ ጣቢያ የድምፅ አሰጣጥ

    የፎቶው ባለመብት, NEBE

    የምስሉ መግለጫ, ሐመር ምርጫ ክልል፣ ቆላጃ አንጉዴ ምርጫ ጣቢያ የድምፅ አሰጣጥ
    የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን የሚመሩት የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ መጀመርን ሲታዘቡ

    የፎቶው ባለመብት, ETV

    የምስሉ መግለጫ, የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን የሚመሩት የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ መጀመርን ሲታዘቡ
    የኢጋድ ምርጫ ታዛቢዎች ቡድን በጅማ ተገኝተው የድምጽ አሰጣጥ አጀማመሩን ሲከታተሉ

    የፎቶው ባለመብት, EBC

    የምስሉ መግለጫ, የኢጋድ ምርጫ ታዛቢዎች ቡድን በጅማ ተገኝተው የድምጽ አሰጣጥ አጀማመሩን ሲከታተሉ
    በአፋር ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳ የድምፅ አሰጣጡ ሂደት የተጀመረው ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ነው

    የፎቶው ባለመብት, EBC

    የምስሉ መግለጫ, በአፋር ክልል አርጎባ ልዩ ወረዳ ድምጽ የሚሰጡ መራጮች
    የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ድምፃቸውን ሲሰጡ

    የፎቶው ባለመብት, EBC

    የምስሉ መግለጫ, የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ድምፃቸውን ሲሰጡ
  3. የኢትዮጵያ ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው

    ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ መራጮች በድምጽ መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት መምረጥ ጀምረዋል

    የፎቶው ባለመብት, FBC

    የምስሉ መግለጫ, ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ መራጮች በድምጽ መስጫ ጣቢያዎች በመገኘት መምረጥ ጀምረዋል

    ከትግራይ ክልል በስተቀር በመላ አገሪቱ በሚካሄደው ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ድምጽ መስጠት ተጀምሯል።

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ እና በአማራ ክልል ደግሞ በተወሰኑ አካባቢዎች ምርጫው በዛሬው ዕለት እንደማይካሄድ ቀደም ብሎ አስታውቋል።

    ምርጫ ቦርድ በአማራ ክልል በስምንት የምርጫ ክልሎች በዛሬው ዕለት ድምጽ እንደማይሰጥ ሲያሳውቅ ከጠቀሳቸው ቦታዎች መካከል ደቡብ እና ምዕራብ ጎንደር፣ ደጋ ዳሞት እና አምባሰል ይገኙበታል።

    በሰባተኛው አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ከ 54 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ቦርዱ መግለጹ አይዘነጋም። በምርጫው የሚሳተፉ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲሆኑ ፓርቲዎቹ ከ10,000 በላይ እጩዎች ለማስመረጥ አስመዝግበዋል። ከእነዚህ ውስጥም 2,080 ለፓርላማ የሚወዳደሩ ይሆናል። 8,352 እጩዎች ደግሞ ለክልል ምክርቤት ሲዎዳደሩ፤ 80 እጩዎች በግላቸው ይወዳደራሉ። 55 የአገር ውስጥ ሲቪክ ማኅበራት ምርጫውን የሚታዘቡ ሲሆን የአፍሪካ ኅብረት በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የሚመራ የታዛቢ ቡድን አሰማርቷል።

    የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የምርጫ ታዛቢ ቡደንን የሚመሩት ደግሞ ቀድሞው የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት ስፔሲዮሳ ዋንድሬ ካዚምብዌ ናቸው።